የመሬት ሊዝ ጨረታ 2ተኛ ዙር ውጤት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 🇪🇹
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስድስት ዓመታት ውስጥ ያወጣው 2ኛው የመሬት ሊዝ ጨረታ ውጤት ወጥቶ ተመለከትነው።
በጨረታው ውጤት መሰረት ዝቅተኛው ለካሬሜ የተሰጠው ዋጋ 20,100ብር ሲሆን ከፍተኛው የአንድ ካሬሜ 470,000ብር በወሎ ሰፈር አካባቢ ለወጣ አንድ ብቸኛ ቦታ መሆኑን አይተናል።
ከወሎ ሰፍሩ ትልቅ ዋጋ በመቀጠል በፒያሳ የወጡ ቦታዎች እስከ 350,000ብር የተሰጠባቸው ሲሆን በአከፋፈል ሁኔታ የፒያሳው ትልቁ አሸናፊ የአንድ ካሬሜ ዋጋ 311,000 ሆኖ ተገልጿል።
ትላልቆቹ ዋጋዎች ላይ ብዙ ተወራባቸው እንጂ በሌሎች ክፍለከተማዎች ብዙዎች አሸናፊ የሆኑበት ዋጋ በግንቦት 2015ዓም አሸናፊዎች በንጽጽር የዘንድሮ አሸናፊዎች በተሻለ ዋጋ እንዳሸነፉ መረዳት ይቻላል።
ከአምናው የሊዝ ጨረታ ጋር ንጽጽራችንን ስንቀጥል ባለፈው ጨረታ ለ297 ቦታዎች 20,636 ሰዎች የጨረታ ሰነድ ገዝተው 11,437 ሰነድ አስገብተው ተጫርተው ነበር። ዘንድሮ ለ243 ቦታዎች 4201 ሰዎች ሰነድ ገዝተው 2972ብቻ ሰነድ ሞልተው አስገብተው ተጫርተዋል።
ባለፈው የሊዝ ጨረታ አሸናፊ ከሆኑት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ውል የተዋዋሉት ከ50% በታች ማለትም 131አሸናፊዎች ብቻ ነበሩ። የዘንድሮው ከአስር የስራ ቀናት በኋላ የሚታይ ይሆናል።
የዘንድሮ ከፍተኛው የካሬሜ ዋጋ ብር 470,000 በቂርቆስ ክ/ከ ወሎ ሰፈር አካባቢ የተሰጠ ሲሆን የአምናው ከፍተኛ አሸናፊ 414,000ብር ለካሬሜ በአራዳ ክ/ከ ነበር። የዘንድሮው ከፍተኛው የአራዳ ክ/ከ ዋጋ 311,000 ፒያሳ አካባቢ ለወጣ ቦታ ተተሰጠ ነው።
በሁለቱም ዙሮች የተሰጡት አነስተኛ ዋጋ ተመሳሳይ ለካሬሜ 20ሺ ብር ነው።
የመሬት ነገር መሬት እየነካ ይመስላል ።
Comments
Post a Comment