Skip to main content

Posts

Featured

የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ ይችላል?

 የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ ይችላል? * **** "ቤት አትግዙ " የሚል የሶሻል ሚዲያ ቻሌንጅ የማከብረው ወዳጄ ልኮልኝ ተመለከትኩ። አላማው በደምሳሳው ቤት ውድ ስለሆነ እስኪቀንስ ድረስ አትግዙ የሚል ነው...ይሄ ብዙም ውጤታማ ሊሆን የማይችል ቻሌንጅ እንደሆነ ቢታወቅም ሀሳቡ ግን የሚበረታታ  አይደለም ምክንያቱም ስሁት ነው። የሪል እስቴት ዘርፍን በቅጡ ካለመገንዘብ የመጣ ቤት ተወዷል ብሎ ለውድነቱም አልሚዎችን ብቻ ተወቃሽና ተከሳሽ ለማድረግ የታሰበ የችግሩን መሰረት ያልተረዳ ነው።  እስኪ የዘርፉን አሰራርና ችግሩን እንድንረዳ ስለ ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዋና ተዋናዮችና አስተዋጽኦዋቸው ጥቂት እንበል።  ሀ) ባለድርሻ አካላትና ድርሻዎቻቸው * * የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አምስት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት አሉት። የሀገራችንን ሁኔታ ታሳቢ አድርገን ስናቀርበው ከዚህ በታች የተገለጸውን ሊመስል ይችላል:- ፩) አልሚ (Developer) :- ስራ ፈጣሪ ነው፣ መሬትን ወደ ውጤታማ የሆነ ተፈላጊ የመኖሪያ ስፍራ በመቀየር ትርፍን የሚያገኝ መላ ፈጣሪ ነው፣ የገንዘብ አምጪ፣ የኪሳራሃላፊነት ወሳጅ፣ ቀጣሪ ሲሆን ዓላማው የገንዘብ ትርፍ ማግኘት፣ የቤት ችግር መቅረፍ ቢዝነሱ ያደረገ፣ ዘላቂ ንብረት ማፍራት፣ ጥሩ ስም መገንባት ... ፪) መንግስት(public organization):- መንግስት ዜጎች ቤት እንዲያገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን ያወጣል፣ ለቤት ልማት የሚሆን መሬት ያቀርባል፣ የግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ የግብይት ሂደቱን ይቆጣጠራል.... በሪል እስቴት ልማት ውስጥ የመንግስት ዋና ፍላጎት  የልማቱ ሂደት በስኬት ተከናውኖ   ዜጎች ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣  የህዝብ ሃብት የሆነው መሬት በ...

Latest Posts

የሪል ስቴት ገበያው እንዲሰክን አድርጓል!

የመሬት ሊዝ ጨረታ ሀምሌ 2016 / 2024

የመሬት ሊዝ ጨረታ 2ተኛ ዙር ውጤት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 🇪🇹

የቤት ኪራይ አዋጅ 🏠 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 🇪🇹

ተጠንቀቁ 🏠 ሪል እስቴት ስንገዛ *22🤔?*

የቤት ባለቤት ይሁኑ ዲኤምሲ DMC Real Estate

📌ማስጠንቀቂያ 📌 ከፈንጅ አምካኝ ቀጥሎ ከስህተት ሊማሩበት የማይቻለው የቤቶች ግብይት ነው ይባላል

Welcome to Zoble bet 🏠 እንኳን ወደ ዞብል ቤት በደህና መጡ